ሰበር ዜና የኮሜቴዎቻችን ጠበቆች ፊልም እንዴታገድ በዛሬው 27-05-2005 እለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት እንዲታገድ አቀረቡ

ETV Special Program – Terrorism and its danger – A preamble to Jihadawi Halekat | February 04, 2013

የኮሜቴዎቻችን ጠበቆች ፌልሙ እንዴታገድ
በዛሬው
27-05-2005 እለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/
ቤት አራተኛ ወneጀል ችሎት እንዲታገድ
አቀረቡ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች ጠበቆች ኢቲቪ ማክሰኞች ምሽት “ጂሀዳዊ ሀረካት በሚል ርእስ ” አቀርበዋለሁ በሚል እያስነገረ ያለውን ዘጋቢ ፊልም ተቃወሙት እንዳይተላለፍም ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የኮሚቴዎቹ ጠበቃ ለቪኦኤ እንዳስረዱት ኢቲቪ ከዚህ ቀደም የችሎት ውሎን አጣሞ በመዘገቡ ከችሎት እንዲወጣ ዳግመኛም ችሎቱን እንዳይታደም እቀባ እንዲደረግበት ጥያቄ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ከችሎት እንዲወጡ ማድረግ እንደማይችል ግልፆ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ኢቲቪ ዘገባውን ሚዛናዊ እንዲያደርግ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፤ ነገርግን ይህንን የፍድ ቤት ትእዛዝ ያከብራል ተብሎ ሲጠበቅ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ እንደገና በመጣስ ወደ አንድ ወገን ያደላ፤ የደንበኞቻችንን ከፍርድ በፊት ንፁህ ሰው ተደርገው የመገመት ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ ትግባር በኢቲቪ እየተፈፀመ ነው፡፡ የኢቲቪ ተራ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ አሁን ባለው የማስታወቂያ ደረጃ እንኳን ደንበኞቻችንን ሳይኮሎጂ የሚጎዳ በህዝብ ዘንድ ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ እንዲታዩ የሚያደርግ ተግባር ስለሆነ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪ እቲቪ አቀርበዋለሁ ያለው የሀሰት ድራማ ተከሳሾቹ በማእከላዊ እያሉ እጅግ አሰቃቂ ድብደባ እና ማሰቃየት፤ በዛ ግቢ(ማእከላዊ ) ውስጥ ይፈፀማል የማይባል የሰቆቃ ተግባር ተፈጽ ሞባቸው ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርገው እንዲናገሩ ተገዱበትን ቪዲዮ ለማቅረብ ነው ያሰበው ፡፡ ይህ ድርጊት የፍርድ ቤቱን ነፃነት እና ገለልተኛነት አደጋ ውስጥ የሚከት ሲሆን በተከሳሾች ላይ ደግሞ የማይተካ ጉዳት ያመጣል ብለዋል፡፡
ጠበቃው የኢቲቪ ፕሮግራም እንዳይተላለፍ ለፍርድ ቤት የጽሁፍ ማመልከቻ ማገባታቸውን፤ከዳኞቹ መሀከል አንድ ዳኛ በጽፈት ቤታቸው የእግድ ጥያቄውን ማንበባቸውን ገልፀው ሆኖም፤ ሌሎች ዳኞች በጽፈት ቤታቸው ስላልነበሩ ዳኛው ብቻቸውን መወሰን የማይችሉ በመሆኑ ነገ ጠዋት አቤቱታቸውን በችሎት እንደያቀርቡ የተነገራቸው መሆኑን ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡ አይዘውም ምስክርነት የመስማት ሂደቱ ለጋዜጠኞች፣ለዲፕሎማቶች፣ ለቤተሰቦች እንዲሁም የፍትህ ስርአቱን ለሚከታተሉ የሰብአዊ መብት ታጋዮች፤ እና ለህብረተሰቡ ስውር በሆነበት ሁኔታ በኢቲቪ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይላቸው ህዝብ ዘንድ ስማቸውን ማጠልሸት ከባድ የህገመንግስት ጥሰት መፈጸም ነው በማለት ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡
በዚህ መሰረት እነ አቡበክር አህመድ
በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳዩ
በክርክር ላይ ያለ መሆኑ ይታወቃል ነገር ግን
ኢትቪ በነገው ምሽት ሁለት ሰዓት ተከሳሾችን
በተመለከተ
< ጅሃድ ሀረካት> በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ
ፌልም አዘጋጅቶ ሊያቀርብ መሆኑን በመገናኛ
ብዙሃን እያስተዋወቀ ይገኛል ክርክሩ በፍ/ቤት
እየተካሄደ ባለበት ጊዜ ይህ ፌልም በመቅረብ
1 ተጠርጣሪዎች ከፍ/ቤቱን በፌት ነፃ ሆኖ
የመገመት ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ
ነው
2 የክቡር ፍ/ቤቱን ነፃና ገለልተኛነትን የሚጋፋ
ነው ፍ/ቤቶንም መዳፈር ነው
3 ፌልሙን የሚመለከተው ህብረተሰብ
ተከሳሶችን ጥፋተኛ ከሆነ በፍርድ ነፃ ቢወጡ
እንኯን ሊካስና ሊተካ የማይችልና የማይመለስ
ጉዳት ይደርስባቸዋል
4 ተከሳሾቹ ተከላከሉ ቢባል የመከላከያ
ምስክሮችን አቅርበው እንዳይሰሙ ትልቅ
ተፅዕnu ያሳድራል በዚህም የፍትህ መዛባት
ይደርሳል
5 ፌልሙ ሊቀርብ የታሰበውም ሚዛናዊነቱን
ሳይጠብቅ ማለትም ተከሳሾቹ
ስለሚያቀርባቸው ጉዳቶ አስተያየታቸውን
እንዲሰጡ ሳይጠይቅና ሳይፈቅዱ በመሆኑም
የፕሩስ ህጉን በግልፅ የሚጥስ ነው ስለሆነም
ኢትቪ ሊያቀርበው ያሰበውን ዶክመንተሪ
ፌልም እንዳይቀርብ እና ይህንንም ለማቅረብ
በመገናኛ ቡዙሃን እያካሄደ ያለው የማስተዋወቅ
ተግባር እንዴያቆም የእግድ ትዕዛዝ
እንዲሰጥልን ክቡር ፍ/ቤቱን እንለምናለን
የተከሳሽ ጠበቆች

posted by Aseged Tamene

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s