የኢትዮጵያ ርቮሊሽን ጃዋር ዋንጫ !

21 July 2013 at 23:07

ወያኔ የኢትዮጵያን ፒሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ብሎ ሲሰይም ሰላማዊ ዘጎችን ለማሰር እና ለመግደል ደግሞ ጃህዳዊ ሃረካት ፣ የሳራ በረሃዉ ጉዞ እና የመሳሰሉ ዶክመንተሪ ፊልሞችን በመስራት ሲያስቀን ኑሯል፡፡  የባሰ አለና ሃገርህን አትልቀቅ አሉ !

ዛሬ ያለነዉ እፈረንጆቹ አገር ነው ፡፡ የሰዉ ዘር አመለካከት ከትላንትናው የተሻለ መሆኑን አለ መቀበል አትችልም የምትጠቀምበት ቁሳቁስ ፣ የሰዉ ልጅ የደረሰበት የተክኖሎጂ ጣሪያ ፣ የሰዉ አገር ሰዉ የሚተዳደሪበት የፖለትካ ስርዓት ይህ ሁሉ ያሳብቅብሃል ፡፡

ጎበዝ ቆም ብለህ አስብ አስቲ !! እኔን ካልሆንክ ብሎ ለቅሶ ፣ እኔ አዉቅልሃለሁ ፣ የእኔ ይሻልሃል ብሎ ጫወታ መጫወት የሚፈልግ የሰዉ ዘር በዚህ ዘመን መኖሩን ስታይ በየትኛው ዘመን ላይ እንዳለህ ራስህን መጠየቅህ አይቀርም ፡ ይገርማል በዚህ ዘመን እንዃን የሰዉ ልጅ አህያም ” እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል “አባባል የኔ አይደለም ማለትዋ አይቀርም፡፡

እኔ የምለዉ የጊዜ አቆጣጠራቸው ወደ ኃላ መንከርፈፉ ከአእምሮ እድገት ለዉጣቸዉ ጋር ይዛመድ ይሆን እንዴ ? ያስብላል፡፡

ነገሩ ውዲህ ነዉ ፣ ጃዋር በአልጀዚራ ማንነቱን ተጠይቆ ኦሮሞ ነኝ ማለቱን አስመልክቶ በተለያዩ የሃበሻ ሜዳዎች ለክብሩ የጀዋር ዋንጫ ጫዋታ ደርቶአል፡፡

ኢሳትን የመሳሰሉ የአማራ ሚዲያዎች ከሊቅ እስከ ደቂቂ ስያስመክሩ ሰንብተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተራዉም ህዝብ ጋዜጠኛ፣ ሁሉም ሃበሻ የፊልም አቀናባሪ ሆነዋል ፡፡ የወያኔዉ አልበቃ ብሎን በየቀኑ ጃዋራዊ ሃረካት የተሰኘ ፊልም እየሰሩ ያዝናኑናል ፡፡ አይ ሃበሻ የዘሬን ከተዉኩ ያንዘሪዝረኝ መሆኑ ነዉ፡፡

ታድያ ተጫዋቹም ደጋፊዉም ዳኛውም ኣራጋቢውም ሁሉም ሃበሾች ናችዉ፡፡ የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ ተጫዋች እና አራጋቢ የራሳችዉን እና የተቃራኒዉን ቡድን ሜዳ እና ጎል እንዃን መለየት የማይችሉ እንከፎች መሆናችው ነዉ፡፡

በባዶ ሜዳ እርስ በርሳችዉ እየተጠላለፉ ይወድቃሉ፣ የጫወታ ታሪካችዉን ብታገላብጥ ሽወዳና ታክል ይበዛዋል፡፡ ጎል ላይ ባዶ ናችዉ፡፡ ከባለፈዉ ስህተታችዉ አይማሩም እንደ ጀግንነት ያወሩታል ፡፡ በእንደዚህ አይነት ተጫዋቾች የተገነባዉ የኢትዮጵያ ቡድን ላለፉት መቶ አመታት ዃስዋን በቁጥጥሩ ስር ብያደርገዉም አንድ የሚረባ ጎል ሳያስመዘግብ አሳፋሪ የታሪክ ጠባሳ ትቶ አልፎአል፡፡

በአለም የጫወታ ህግ አዉቀህ ጥፋት ማጥፋት አይደለም ሙከራ ማድረግ በራሱ ያስቀጣ ል ፡፡ ታዲያ የጀዋር ዋንጫ ጫወታ በተጀመረ በሶስተኛዉ ሳምንት በቀደም የተደረገዉ አስቀያሚ ጥፋት ግን በማስጠንቀቂያ ወይም በቢጫ ካርድ የሚታለፍ አይደለም፡፡

ነገሩ እንዲህ ነዉ፣ በጀዋር ዋንጫ ጫወታ ለይ ሃበሾች ዃስዋን ያላግባብ ሲጨማለቁበት ላየ ሰዉ የፊፋ ያለህ የምያስብል ነዉ፡፡

ታድያ አብዲ ፊጤ የተባለ ወጣት ዃስዋን ለጥቂት ደቂቃ ተቆጣጥሮ የጫወታዉ ህግ እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ቢሞክር  ከእነዝያ አራጋቢዎች ሁለቱ ከጫወታዉ ሜዳ ዉጭ ቤታችዉ ገብተዉ ቢላዋ ታጥቀዉ ይህን ወጣ ት ለመግደል ሙከራ ማድረጋችዉን ስሰማ ብዙ አልገረመኝም፣ ጥፋት ከትዉልድ የወረሱት አባዜ ነዉ ብየም አልደመደምኩም ፡፡ የሁለቱ ሰዎች አላዋቂነት ነዉ ብየም ራሴን ማታለል አልዳዳኝም፡፡

እስቲ አለማወቅ ይሆናል ብለን እንለፈዉ፣ ዳሩ ግን እነዚህ ሰዎች ለአለም ዴሞክራሲ እናት በሆነች ሃገር እምብርት ላይ ቁጭ ብለዉ እንደዚህ አይነት ድርጊት መፈፀማችዉ እጀግ አሳዛኝ ነዉ ፡፡የትም አገር ቢኖሩ የማይቀየሩ ድንዙዝ መሆናችዉን ትረዳለህ፡፡

ጎበዝ አንዴ ቆም ብሎ ማሰብ የሚችል ሰዉ እንዴት ታጣላቹ ? ወያኔ በፖለትካ አመለካከታችዉ ወገኖቻችንን አሰረብን ገደለብን ብለን ለአለም  ኡ….ኡ…ኡ..ኡ ብለን ስናበቃ የእናንተ ይባስ ! ሰዉን በአመለካከቱ ለመግደል ሙከራ ያዉም በሰለጠነ አለም እየኖራችሁ ታድያ እናንተ የፖለቲካ ስልጣን አይኖራችሁም እንጂ ቢኖራችሁ …. እዉነት እዉነት እላችሗለሁ ምንም አታመጡም!! ሁሌም በራሳችሁ እግር ቆማችሁ በአያቶቻችሁ እራስ የምታስቡ ባዶ ጠርሙሶች ስለሆናችሁ ምንም አታመጡም!!  ከመቶ ዓመት በላይ እናዉቃችሗለን፡፡

እኔ ግን እስከ መች የሞኝ ጫወታ እንደምትጫወቱ አይገባኝም ፡፡ ለምን ጠቆርክ እንደ እኔ አትቀላም ? ኢትዮጵይዊ እኮ ቀይ ነዉ ፣ለምን ወፈርክ እንደ እኔ አትከሳም ኢትዮጵይዊ እኮ ቀጭን ነዉ ፣ለምን ረዘምክ እንደ እኔ አታጥርም ኢትዮጵይዊ እኮ ኣጭር ነዉ ፣እያላችሁ መጃጃልን አቁሙ !!! ኢትዮጵያንም የራሳችሁን አሮጌ ጥብቆ ልታለብስዋትጊዜአችሁን አትፍጁ፡፡

ሰዎች ! የእናንተ ፖለቲካ መልሱም ሎጂኩም ቀላል ነው ፡፡ አንተ እኔን ካልሆንክ አንተ አንተን ልትሆን አትችልም. የአንተነትህ መስፈሪያ ሁሌም እኔ ነኝ ነው፡፡እኔ ግን እላችሗለሁ እኔ እኔ ነኝ ! አንተ አንተ ነህ ! እሱ እሱ ነዉ ! ሁሉም ሰዉ አማራ ሊሆን አይችልም! በቃ ይሔዉ ነዉ ጨረስኩ ለዛሬ ይብቃኝ ሰላም ሁኑ፡፡

ከሀዩ ቀናቴ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s